Posts

Showing posts from October, 2020

ስንፍና

Image
  ስንፍና እግሬ   ሽባ   ሆነ   መራመድ   የማይችል መሄድ የተሳነው እራስን ማስመለጥ  ተጋድሞ የማይነቃ ነቅቶ የሚንቀጠቀጥ አካሌ ብርክ ያዘው  . . . ጡንቻዎቼ ፈሱ አልችል አሉ ዳገት ሟሙ፣ ጣምራቸው ተፈታ ላሉብኝ በድንገት። መቅኒዬ ካጥንቴ ዘይቴ ከሎሚ ፈሰሱ ፈረሱ ኣካሌ ተጣላ እራሱን በራሱ።  እጄ ዛለ ተኛ አልታዘዝ አለ ከዚህ፣ ከመገጣጠሚያው ወልቆ እንደተጣለ ጣቶቼን ማዘዙ ሆነብኝ ተራራ በዛብኝ መዘዙ። ስንፍና. . .  ከጣለኝ ቦሃላ ካስተኛው አካሌን  ደግሞ እንዳልነቃ እንዳላዝ ብልቴን ራሴን እንድጠላ አካል ብቻ እንድወድ  ባ’ምሮት ጂ በእውነት ከቶ እንዳልገደድ  ካ’ረገኝ በኋላ ህልም እየመሠለኝ ደግሞም እንደቅዥት እራሴን በራሴ አልታዘዝ ማለት ክፉ እየመጣብኝ ሸሽቶ አለመገኘት  በለመድኩት ክፋት  በበላሁት ጠኔ ስንፍና ይወግረኛል ልረፍ ባልኩኝ እኔ።   ጥር 12 , 2011  ዓ.ም ሌሊት 9 :00

የምኞት ባሪያ

Image
  የምኞት   ባሪያ በሕይወት ደዌ እንጋረፍ  አካልህን ባካሌ አካሌንም ባካልህ እናናጋ እርካታ በማያውቅ የሥቃይ ጎጆ እንኑር  ላትፈታኝ ላልፈታህ ሥሥት የሌለው ጭካኔ ይጋባን ስግብግብ እንሁን እርስ በእርስ እንቃጭ አንኑር አንደግ የዶግ አመድ ሁነን ደም በደም እንራጭ  እንፋጅ በሰቆቃ እንሙት በ’ንግልት እስክዝል ልነቅህ እስክትዝል እነቀኝ ና እንጨፋጨፍ  ምኞታችን ቁማ እኛን ታጨፋጭፍ ና አብረን እንውደም  እኔ ላሸንፍህ አንተም እኔን እርታ ድቤ እንደባለቅ ከማቾቹ ተርታ ና አብረን እንውደም እኛነታችን እንውጋ ቀንዴን ለሥቃይህ ቀንድህ ለሥቃዬ ይሁነን እንሙት እንውደቅ አንዳችን  እኩይ እንሞላ ይጨለጥ ጽዋችን  የኔ አንገት ጅራፍ ነው ያንተም እንደዚሁ  ና እንጠባሰቅ በሰቆቃ ጅራፍ፤ በማሸነፍ ምኞት ኑሮን ለኔ ብቻ በሚል አይነት ሕይወት ሁሌ እንጠባሰቅ  ሁሌ እንሳቀቅ ሰማይ ተገልብጦ ምድር ትዙርብን አንዳችን ላንዳችን ህመም እየሆንን ስራችን ባንዳችን ኃጢኣት ይሁንብን  እርካታ ጠፍቶበት ሥቃይ ካለው ጎጆ፤ ሞት ይግባ ቤታችን የማሸነፍ ጥማት ካናጋው ኑሮኣችን መከባበር ጠፍቶ ካደገ ሥራችን  እንዳናጎነብስ አንገት እንዳንሠብር ልባችን ካበጠ አላይ ካላ ምድር ካንዱ ገደል ገብተን መሠበርም አይቀር  ስለዚህ ና እንቁሰል ካልቀረ ሞታችን እንቁሰል፤ ቆስለን ደግሞ እናቁስል  በብዙ እንቧጠጥ በብዙ እንጣበስ  ተጠብሰን ተጣብሠን ጠባሳ እንጣጣል። እናታችን ትሙት አባታችን ይጥፋ  ሰዉ ቤት እንደግ ኑሮአችንም ይክፋ ጓደኛ አናግቶን ያልሆነውን እንሁን ታመን አሳምመን በበዳይ ማህበር ይነሳ ጽዋችን በቃ!    በቃ! እንደዛ እንሁን የቆሠሉ ...