ስንፍና
ስንፍና
እግሬ ሽባ ሆነ መራመድ የማይችል
መሄድ የተሳነው እራስን ማስመለጥ
ተጋድሞ የማይነቃ ነቅቶ የሚንቀጠቀጥ
አካሌ ብርክ ያዘው . . .
ጡንቻዎቼ ፈሱ አልችል አሉ ዳገት
ሟሙ፣ ጣምራቸው ተፈታ ላሉብኝ በድንገት።
መቅኒዬ ካጥንቴ ዘይቴ ከሎሚ ፈሰሱ ፈረሱ
ኣካሌ ተጣላ እራሱን በራሱ።
እጄ ዛለ ተኛ አልታዘዝ አለ
ከዚህ፣ ከመገጣጠሚያው ወልቆ እንደተጣለ
ጣቶቼን ማዘዙ ሆነብኝ ተራራ
በዛብኝ መዘዙ።
ስንፍና. . .
ከጣለኝ ቦሃላ ካስተኛው አካሌን
ደግሞ እንዳልነቃ እንዳላዝ ብልቴን
ራሴን እንድጠላ አካል ብቻ እንድወድ
ባ’ምሮት ጂ በእውነት ከቶ እንዳልገደድ
ካ’ረገኝ በኋላ
ህልም እየመሠለኝ ደግሞም እንደቅዥት
እራሴን በራሴ አልታዘዝ ማለት
ክፉ እየመጣብኝ ሸሽቶ አለመገኘት
በለመድኩት ክፋት
በበላሁት ጠኔ
ስንፍና ይወግረኛል ልረፍ ባልኩኝ እኔ።
ጥር 12, 2011 ዓ.ም
ሌሊት 9:00

Comments
Post a Comment