Posts

Showing posts from May, 2022
Image
  ትኩስ ህመም ሳር ቅጠሉ በተኛበት ሰብዓዊ በሞተበት ቤት ደጃፉን በዘጋበት አልጋ ሰውን ባዘለበት በዛች ቅጽበት በዛች ጊዜ . . . ጉብዝና ያላቸው ሙላ አካል የያዙ አካልሽን ተካፍለው ባንቺ ስም የገዙ አዕምሮኣቸው ሰሎ የተጎነደሹ እንዲያ የቆሸሹ ለመጽዳት . . . ዱሻቸውን ታጥበው በዱሽ ተመገቡ ደግሞ አንቺን ዳሰሱሽ ነክተው አቆሸሹሽ በቁራጣ እጃቸው አንቺን አረከሱሽ በዱሽ ደግሞ አጠቡሽ ተነሳ ቅርፊትሽ ውበት ደም ግባትሽ . . . ተጣሰ ህግጋትሽ ጉልበታቸው ሳይዝል ጉልበታም እንዳሉ አዕምሯቸው ደክሞ ማሰብ እንዳልቻሉ እጆች እያላቸው በዱሽ አንቺን በሉ አንቺንም አበሉ ያለ ፍላጎትሽ ያለ አንዳች መሻትሽ በዱሽ ጎረስሽና ሳትረኪ ጠገብሽ ይኸው ገፍ ሆድሽ ያመኛል አሞኛል ታምሜያለው እያልሽ. . . ምግቡ የገባበትን ጉሮሮ እየቧጠጥሽ ትተንፍሺ ዘንድ እንዲያስመልስሽ ቧጠሽ አስወግደሽ ሌላ ትኩስ ህመም ህመምሽ ላይ ጨመርሽ ሌላ ትኩስ አፈር ካፈር ጋር ቀላቀልሽ።       20/6/2008 ዓ.ም

አላሸንፍህም

Image
  አላሸንፍህም   እ ፋለ ም ሃለ ው እታገልሃለው እፋተግሃለው ጎኔ እስኪቆስል ሸካራው አካሌ ላንተ እስኪለሰልስ ጉጠቴ እስኪለቅ በጎን ያበቀልኩት ስታቀፍ የወጋህ     ካ’ካሌ ተሰብሮ ከላዬ እስኪወድቅ እተሻሽሃለው ትዕቢት ወጥሮት መሬት በግንባሩ ቆፍሮ ቆፍሮ አፈሩን ባ’ናቱ እንደሚነሰንስ ገጣሚ ፈልጎ ቀዬ እንደሚረቢሽ እንደ አበያ በሬ ጉልበት እንደሞላው እንዳልተጠመደ እንደ ጎበዝ ወይፈን ቀንበር አልይዝ ብዬ አስቸግርሃለው ደሞ አጎነብስና ውግያ እገጥማለሁ አንተኑ ወግቼ ካንተ ላይ ቦጭቄ አንተን በአናቴ እስክነሰንስህ እታገልሃለው እፋለምሃለው ባላሸንፍህም እፋተግሃለው ፠፠፠፠፠፠፠፠ ≤≥ ፠፠፠፠፠፠፠፠ ትናጋውን ይዞት ህቅ እንቅ እንዳለው እንባ እንደጠመቀው ትዕቢት እንደሞላው እንደጨቅላ ጩጬ ታላቁ ጋር ገጥሞ እንደሚለፋደድ ሰንዝሮ ሲማታ አየር እንደሚዝቅ ኢላማ   እንደሳተ እንደሚዘባርቅ ተነስቶ እንደሚወድቅ መቆም እንደማይችል እንደተላላጠ አደጋ እንዳገኘው ሰውነቱ ደቆ አካሉ ተላቆ መቆም እንደማይችል ምርኩዝ ተደግፎ መሮጥ እንደማይችል ተዘርሮ ወድቆ መነሳት እንዳይችል እንደተሰበረ መረታቱን አምኖ እንዳቀረቀረ መሣሪያ   እንደሌለው እጁ እንደማየሠራ ከበው እንደያዙት ብቸኛ ወታደር እንዲያ እስክሆን ድረስ እንዲያ እስክሆን ድረስ እታገልሃለው። እፋለምሃለው። መቆም እንዳልቻለ ራሱን እንደሳተ ኃሳቡን ለመግለጽ እንደሚንተባተብ እንደተለጎመ ቃላት እንደጠፋው እንዲያ እስክሆን ድረስ ባላሸንፍህም እታገልሃለው እታገልሃለው እፋለምሃለው። ቃልህ እንደሰደፍ ጎኔን አንቆራጦ መተንፈሻ አጥቼ...

Perception of My life

Image
I sometimes feel like this I fight myself I have no idea to which idea should I side And make peace with me. I struggle with it One side of me suggest not to be caring Loving, dependent The other says no Be a loving caring and dependent person. The other speaks with anger Fuck life! Fuck everything about it. Fuck selfless You don’t need it. You just need to be you No one cares about you Everyone has a million reason not to care for you So build your reason   "No man don’t say that!" says the other me It suggest that I need to be The good guy That I should be a reason for others to life A reason for who (says the other me) Bruh you are fucked up No one has been a reason for your survival Everyone whom you lived with Have a coffee with People whom you shared a meal with All of them They were an asshole to you. So go get your life Live for yourself. The other speaks in a calm and mannered way Yeah you may be right But also Everybody he has meal with Or had a cup of tea People wh...