Posts

Image
  ትኩስ ህመም ሳር ቅጠሉ በተኛበት ሰብዓዊ በሞተበት ቤት ደጃፉን በዘጋበት አልጋ ሰውን ባዘለበት በዛች ቅጽበት በዛች ጊዜ . . . ጉብዝና ያላቸው ሙላ አካል የያዙ አካልሽን ተካፍለው ባንቺ ስም የገዙ አዕምሮኣቸው ሰሎ የተጎነደሹ እንዲያ የቆሸሹ ለመጽዳት . . . ዱሻቸውን ታጥበው በዱሽ ተመገቡ ደግሞ አንቺን ዳሰሱሽ ነክተው አቆሸሹሽ በቁራጣ እጃቸው አንቺን አረከሱሽ በዱሽ ደግሞ አጠቡሽ ተነሳ ቅርፊትሽ ውበት ደም ግባትሽ . . . ተጣሰ ህግጋትሽ ጉልበታቸው ሳይዝል ጉልበታም እንዳሉ አዕምሯቸው ደክሞ ማሰብ እንዳልቻሉ እጆች እያላቸው በዱሽ አንቺን በሉ አንቺንም አበሉ ያለ ፍላጎትሽ ያለ አንዳች መሻትሽ በዱሽ ጎረስሽና ሳትረኪ ጠገብሽ ይኸው ገፍ ሆድሽ ያመኛል አሞኛል ታምሜያለው እያልሽ. . . ምግቡ የገባበትን ጉሮሮ እየቧጠጥሽ ትተንፍሺ ዘንድ እንዲያስመልስሽ ቧጠሽ አስወግደሽ ሌላ ትኩስ ህመም ህመምሽ ላይ ጨመርሽ ሌላ ትኩስ አፈር ካፈር ጋር ቀላቀልሽ።       20/6/2008 ዓ.ም

አላሸንፍህም

Image
  አላሸንፍህም   እ ፋለ ም ሃለ ው እታገልሃለው እፋተግሃለው ጎኔ እስኪቆስል ሸካራው አካሌ ላንተ እስኪለሰልስ ጉጠቴ እስኪለቅ በጎን ያበቀልኩት ስታቀፍ የወጋህ     ካ’ካሌ ተሰብሮ ከላዬ እስኪወድቅ እተሻሽሃለው ትዕቢት ወጥሮት መሬት በግንባሩ ቆፍሮ ቆፍሮ አፈሩን ባ’ናቱ እንደሚነሰንስ ገጣሚ ፈልጎ ቀዬ እንደሚረቢሽ እንደ አበያ በሬ ጉልበት እንደሞላው እንዳልተጠመደ እንደ ጎበዝ ወይፈን ቀንበር አልይዝ ብዬ አስቸግርሃለው ደሞ አጎነብስና ውግያ እገጥማለሁ አንተኑ ወግቼ ካንተ ላይ ቦጭቄ አንተን በአናቴ እስክነሰንስህ እታገልሃለው እፋለምሃለው ባላሸንፍህም እፋተግሃለው ፠፠፠፠፠፠፠፠ ≤≥ ፠፠፠፠፠፠፠፠ ትናጋውን ይዞት ህቅ እንቅ እንዳለው እንባ እንደጠመቀው ትዕቢት እንደሞላው እንደጨቅላ ጩጬ ታላቁ ጋር ገጥሞ እንደሚለፋደድ ሰንዝሮ ሲማታ አየር እንደሚዝቅ ኢላማ   እንደሳተ እንደሚዘባርቅ ተነስቶ እንደሚወድቅ መቆም እንደማይችል እንደተላላጠ አደጋ እንዳገኘው ሰውነቱ ደቆ አካሉ ተላቆ መቆም እንደማይችል ምርኩዝ ተደግፎ መሮጥ እንደማይችል ተዘርሮ ወድቆ መነሳት እንዳይችል እንደተሰበረ መረታቱን አምኖ እንዳቀረቀረ መሣሪያ   እንደሌለው እጁ እንደማየሠራ ከበው እንደያዙት ብቸኛ ወታደር እንዲያ እስክሆን ድረስ እንዲያ እስክሆን ድረስ እታገልሃለው። እፋለምሃለው። መቆም እንዳልቻለ ራሱን እንደሳተ ኃሳቡን ለመግለጽ እንደሚንተባተብ እንደተለጎመ ቃላት እንደጠፋው እንዲያ እስክሆን ድረስ ባላሸንፍህም እታገልሃለው እታገልሃለው እፋለምሃለው። ቃልህ እንደሰደፍ ጎኔን አንቆራጦ መተንፈሻ አጥቼ...

Perception of My life

Image
I sometimes feel like this I fight myself I have no idea to which idea should I side And make peace with me. I struggle with it One side of me suggest not to be caring Loving, dependent The other says no Be a loving caring and dependent person. The other speaks with anger Fuck life! Fuck everything about it. Fuck selfless You don’t need it. You just need to be you No one cares about you Everyone has a million reason not to care for you So build your reason   "No man don’t say that!" says the other me It suggest that I need to be The good guy That I should be a reason for others to life A reason for who (says the other me) Bruh you are fucked up No one has been a reason for your survival Everyone whom you lived with Have a coffee with People whom you shared a meal with All of them They were an asshole to you. So go get your life Live for yourself. The other speaks in a calm and mannered way Yeah you may be right But also Everybody he has meal with Or had a cup of tea People wh...

Telling the truth to one another

Image
  Telling the truth to one another   One of the greatest challenges in life is to seek, find, and apply truth. Understanding the truth is a path to become a healthy, whole, and fruitful person. Aligning with the truth permits a better person in relationships to eventually emerge from within. In life people need to live in peace with others. A person is designed to be in a relationships. 1 The relationships are horizontally with other fellow humans and vertically with God. These are the relationships that gives a person a freedom to be authentic. Truth is a very essential thing to be free. Telling the truth to one another is a way to build an authentic relationship. Truth is one thing that makes us free. One of Jesus’ teachings is “You will know the truth, and the truth will set you free.” 2 No matter what is happening, telling truth to one another makes a person to be believed and build trust. That really helps to share the mission of God. The world suffers a lot, not b...

♥♥ እከኪሊኝ ♥♥

Image
♥♥   እከኪሊኝ    ♥♥ ለምኛት እንድታከኝ                  ለምኛት ታክኬ ወገቤ ቆሰለ              ጥፍሯን ተፎትኬ፡፡ ✈✈✂✂✈✈✂✂✈✈                           © ✍✍አስቻለው ደምስ                                   ሚያዝያ, ፳፪, ፳፻፲ ✉✉✉    መልዕክቴ   ✉✉✉ እስኪ ብዙ ቁስሎቻችሁን እንዴት እንደምታክሟቸው ዘወር በሉና አስቡ፡፡ ሰው ለበላው አካሉ ሁሉ ጥፍሩን ከሰደደ በጎም አይሆን፡፡ ሰው ጥፍራም ስለሆነም አያክም እንዲሁም አያሳክክም፡፡ እምናከውንና እምናሳክከውን እንምረጥ፡፡ እየተከካከክን ከሄድን አንቆሳሰል፡፡ . . .አንዳዶቻችን ለምነን፣ ሌሎኞቻችን ተገደን፤ ደግሞ ከአንዳዶችና ከሌሎኞች የተረፍን ተለምነን ታከናል፡፡  ሲገባኝ ግን እከክ የቆሻሻ ውጤት ነው፡፡ እከክን አስወግደን እንኑር፡፡ #እንፅዳ!!

እንገንጠል

Image
  በአንድ ወቅት በዓዲግራት ከተማ በማገለግልበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በየሳምንቱ የተለያዩ ድራማዎች እንሰራ ነjበር። በእኒህ ወቅት ስንቅር ብለው ከቀሩልኝ ድራማዎች መካከል የአካል ግንድ በመሆን የሰራሁት ድራማ ዋነኛው ነው። የዚህ ድራማ ጭብጥ አካላት ሁሉ የተሠኩበት የአካላቱ ግንድ በድንገት ጥያቄ ይቀርብለታል። የእንገንጠል ጥያቄ። የአካሉም ግንድ ጥያቄአቸውን በሠማ ጊዜ በእጅግ ይደነግጥና ምላሽ መስጠት ይጀምራል። ምላሹንም “ለምን?” በሚል ጥያቄ ይመልሳል። አካላቱም አንድ በአንድ እየተነሱ መመለስ ይጀምራሉ። እኔም ትንሽ እርማት ጨምሬበት አቅርቤዋለሁ። ከተናጋሪ አካላቱ መካከል አንዷ ምላስ ነበረች። “እኔ እኮ    አይጣል። አይጣል ያለኝ ተሰጥኦ። ስንቱን ግብግብ እንዳረኩ። ቅመሺ ስትለኝ ስቀምስ። ተናገሪ ስትለኝ ስቀምስ። ከአፍ የሚወጣ ጂ ወደ አፍ የሚገባ ጣጣ የለውም። አያረክስም! እየተባባልን። ያልተጋትኩት የለም። ደሞ እንደአንዳንዶች እንኳ የሚደረግ ጥቅማ ጥቅም የለኝ። ባለፈው ምን ሰማሁ። የአካል ግንድ ምላሱን ለመንከባከብ በየወሩ አዳዲስ ለስላሳ ብሩሾች ከነፈሳሽ ሳሙናው በጅቷል የሚባል ነገር ደረሰኝ። ዶሮን ሲያታሏት አሉ። እንደው አሁን ማን ይሙት ይህ እሙን ነው። ትላለህ? ጆሮህን ፈልግ ብትለኝ እንኳ እኔ አልሠማህም። ጥርስ እያማረበት በሆነው ባልሆነው ሲገጥ እኔ    እርሱ በታጠበበት ውሃ    የስንቱን ነገር ጣዕም እናዳጣሁ አንተ የማይገባህ የኔ ብቻ ችግር ነው። እናም ወስኛለው። ከእንግዲህ በእንዲህ አይነት ጭቆና መቆየት መሰንበት አልፈልግም፤ ለየኝ ድርሻዬ ስጠኝና ልሂድ።” አለች።   “የአካል ግንድ ሆይ? እኔ አድርግ ሂድ ወዳልከኝ ሁሉ ይህ ጭቃ ነው። ይህ እሾህ ነው። ይህ ድንጋይ፣ ኩር...

ስንፍና

Image
  ስንፍና እግሬ   ሽባ   ሆነ   መራመድ   የማይችል መሄድ የተሳነው እራስን ማስመለጥ  ተጋድሞ የማይነቃ ነቅቶ የሚንቀጠቀጥ አካሌ ብርክ ያዘው  . . . ጡንቻዎቼ ፈሱ አልችል አሉ ዳገት ሟሙ፣ ጣምራቸው ተፈታ ላሉብኝ በድንገት። መቅኒዬ ካጥንቴ ዘይቴ ከሎሚ ፈሰሱ ፈረሱ ኣካሌ ተጣላ እራሱን በራሱ።  እጄ ዛለ ተኛ አልታዘዝ አለ ከዚህ፣ ከመገጣጠሚያው ወልቆ እንደተጣለ ጣቶቼን ማዘዙ ሆነብኝ ተራራ በዛብኝ መዘዙ። ስንፍና. . .  ከጣለኝ ቦሃላ ካስተኛው አካሌን  ደግሞ እንዳልነቃ እንዳላዝ ብልቴን ራሴን እንድጠላ አካል ብቻ እንድወድ  ባ’ምሮት ጂ በእውነት ከቶ እንዳልገደድ  ካ’ረገኝ በኋላ ህልም እየመሠለኝ ደግሞም እንደቅዥት እራሴን በራሴ አልታዘዝ ማለት ክፉ እየመጣብኝ ሸሽቶ አለመገኘት  በለመድኩት ክፋት  በበላሁት ጠኔ ስንፍና ይወግረኛል ልረፍ ባልኩኝ እኔ።   ጥር 12 , 2011  ዓ.ም ሌሊት 9 :00