የምኞት ባሪያ

 


የምኞት ባሪያ

በሕይወት ደዌ እንጋረፍ 
አካልህን ባካሌ አካሌንም ባካልህ እናናጋ
እርካታ በማያውቅ የሥቃይ ጎጆ እንኑር 
ላትፈታኝ ላልፈታህ ሥሥት የሌለው ጭካኔ ይጋባን
ስግብግብ እንሁን እርስ በእርስ እንቃጭ
አንኑር አንደግ የዶግ አመድ ሁነን ደም በደም እንራጭ 
እንፋጅ በሰቆቃ እንሙት በ’ንግልት
እስክዝል ልነቅህ እስክትዝል እነቀኝ
ና እንጨፋጨፍ 
ምኞታችን ቁማ እኛን ታጨፋጭፍ
ና አብረን እንውደም 
እኔ ላሸንፍህ አንተም እኔን እርታ
ድቤ እንደባለቅ ከማቾቹ ተርታ
ና አብረን እንውደም እኛነታችን እንውጋ
ቀንዴን ለሥቃይህ ቀንድህ ለሥቃዬ
ይሁነን እንሙት እንውደቅ አንዳችን 
እኩይ እንሞላ ይጨለጥ ጽዋችን 
የኔ አንገት ጅራፍ ነው ያንተም እንደዚሁ 
ና እንጠባሰቅ በሰቆቃ ጅራፍ፤ በማሸነፍ ምኞት
ኑሮን ለኔ ብቻ በሚል አይነት ሕይወት
ሁሌ እንጠባሰቅ 
ሁሌ እንሳቀቅ
ሰማይ ተገልብጦ ምድር ትዙርብን
አንዳችን ላንዳችን ህመም እየሆንን
ስራችን ባንዳችን ኃጢኣት ይሁንብን 
እርካታ ጠፍቶበት ሥቃይ ካለው ጎጆ፤ ሞት ይግባ ቤታችን
የማሸነፍ ጥማት ካናጋው ኑሮኣችን መከባበር ጠፍቶ ካደገ ሥራችን 
እንዳናጎነብስ አንገት እንዳንሠብር
ልባችን ካበጠ አላይ ካላ ምድር
ካንዱ ገደል ገብተን መሠበርም አይቀር 
ስለዚህ ና እንቁሰል ካልቀረ ሞታችን
እንቁሰል፤ ቆስለን ደግሞ እናቁስል 
በብዙ እንቧጠጥ በብዙ እንጣበስ 
ተጠብሰን ተጣብሠን ጠባሳ እንጣጣል።

እናታችን ትሙት አባታችን ይጥፋ 
ሰዉ ቤት እንደግ ኑሮአችንም ይክፋ
ጓደኛ አናግቶን ያልሆነውን እንሁን
ታመን አሳምመን በበዳይ ማህበር ይነሳ ጽዋችን
በቃ!  በቃ! እንደዛ እንሁን
የቆሠሉ አቁሳዮች ሁነን እንጠራ
ቆስለን ቆስለን ሊደርቅ ያለ ግዜ በልቶን እያሳከክነው ቁስላችን ይድማ 
መዳኛ እንጣ እንሁን እንዳሻን እንሙት በእንግልት
በሕይወት ደዌ እንጋረፍ 
አካልክን ባካሌ አካሌንም ባካልህ እናናጋ
እርካታ በማያውቅ የሥቃይ ጎጆ እንኑር 
ላትፈታኝ ላልፈታህ ሥሥት የሌለው ጭካኔ ይጋባን
ስግብግብ እንሁን እርስ በእርስ እንቃጭ
ጥማድ በሬ እንፍታ ና ቀንበር እንስበር 
ሞፈርህ ሞፈሬ ጥቅሙን ሁሉ ይጣ መሬቱ ጦም ይደር
እርፍህ በእኔ ይለቅ የኔም እርፍ አንተ ላይ
እርቅ እንጥላ ተነስ! እንውደም እናውድም አንድላይ
ከሆንን ላይቀር ባንገታችን ቀንበር ጥማድ ከሆንን
ማተም ካለን ባርያ የሚል ላልወደድነው ከተገዛን
እየቆሰልን እናቁስል እየሞትን እንግደል ፍቅር ካላወቅን
ምኞት የፀነሰው. . . ልጅ ሊወለድለት ቀናት ከጎደለው 
 ተወልዶ ጎርምሶ ጡንቻ ከሸፈነው ገዳይ ልጅ ይወልዳል
ገዳይን የሚገል ገዳይ ሊያደርገው 
የምኞትን ባርያ እንዳይናጠቀው።

Comments

Popular posts from this blog

ስንፍና

አላሸንፍህም